https://amh.sputniknews.africa/20260124/3009387.html
ናሚቢያ የኃይል እጥረቷን በዘላቂነት ለመፍታት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለማቋቋም እያጤነች መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ
ናሚቢያ የኃይል እጥረቷን በዘላቂነት ለመፍታት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለማቋቋም እያጤነች መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ
Sputnik አፍሪካ
ናሚቢያ የኃይል እጥረቷን በዘላቂነት ለመፍታት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለማቋቋም እያጤነች መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ"በአፍሪካ ግዙፍ ከዓለም ደግሞ ሦስተኛ የዩራኒየም አምራች እንደመሆናችን መጠን፤ በተለይም ጥሬ ዕቃዎቻችን በዓለም ዙሪያ... 24.01.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-01-24T16:10+0300
2026-01-24T16:10+0300
2026-01-24T16:14+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh.sputniknews.africa/img/07ea/01/18/3009233_0:40:800:490_1920x0_80_0_0_064c55b07deabffd65e701cfd6a0f1a9.jpg
ናሚቢያ የኃይል እጥረቷን በዘላቂነት ለመፍታት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለማቋቋም እያጤነች መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ"በአፍሪካ ግዙፍ ከዓለም ደግሞ ሦስተኛ የዩራኒየም አምራች እንደመሆናችን መጠን፤ በተለይም ጥሬ ዕቃዎቻችን በዓለም ዙሪያ ለኒውክሌር ማመንጫዎች ኃይል እየሆኑ ባለበት ሁኔታ እኛ ከኒውኩሌር ኃይል ልማት ወደ ኋላ ማለት አንችልም" ሲሉ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ካይሬ ምቡዌንዴ በዳቮስ ፎረም ላይ ተናግረዋል። ለዚህም መንግሥት ብሔራዊ የኒውክሌር ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ 60 በመቶ የሚሆነውን ኃይል ከደቡብ አፍሪካ እንደምታስገባና 60 በመቶ በታች የሚሆነው ሕዝቧ ብቻ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንደሚያገኝ አክለዋል።በተመሳሳይ የአነስተኛ ሞዱላር ሬአክተሮችን (አነስተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን) መጠቀም እየተጤነ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል። ናሚቢያ እና ሩሲያ የዩራኒየም ማዕድን ክምችን በተመለከተ በጋራ ለመሥራት ጥር 6 ቀን መወያየታቸውን የሩሲያ የኒውክሌር ኮርፖሬሽ ሮሳቶም ማስታወቁ ይታወሳል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh.sputniknews.africa/img/07ea/01/18/3009233_47:0:754:530_1920x0_80_0_0_3cc44b69b21909cbea91c1eab9c4cdfc.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ናሚቢያ የኃይል እጥረቷን በዘላቂነት ለመፍታት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለማቋቋም እያጤነች መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ
16:10 24.01.2026 (የተሻሻለ: 16:14 24.01.2026) ናሚቢያ የኃይል እጥረቷን በዘላቂነት ለመፍታት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለማቋቋም እያጤነች መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ
"በአፍሪካ ግዙፍ ከዓለም ደግሞ ሦስተኛ የዩራኒየም አምራች እንደመሆናችን መጠን፤ በተለይም ጥሬ ዕቃዎቻችን በዓለም ዙሪያ ለኒውክሌር ማመንጫዎች ኃይል እየሆኑ ባለበት ሁኔታ እኛ ከኒውኩሌር ኃይል ልማት ወደ ኋላ ማለት አንችልም" ሲሉ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ካይሬ ምቡዌንዴ በዳቮስ ፎረም ላይ ተናግረዋል።
ለዚህም መንግሥት ብሔራዊ የኒውክሌር ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ 60 በመቶ የሚሆነውን ኃይል ከደቡብ አፍሪካ እንደምታስገባና 60 በመቶ በታች የሚሆነው ሕዝቧ ብቻ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንደሚያገኝ አክለዋል።
በተመሳሳይ የአነስተኛ ሞዱላር ሬአክተሮችን (አነስተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን) መጠቀም እየተጤነ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል።
ናሚቢያ እና ሩሲያ የዩራኒየም ማዕድን ክምችን በተመለከተ በጋራ ለመሥራት ጥር 6 ቀን መወያየታቸውን የሩሲያ የኒውክሌር ኮርፖሬሽ ሮሳቶም ማስታወቁ ይታወሳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X