በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተቆረጠ የብልት ክፍልን በረቀቀ የቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ በመቀጠል አዲስ የሕክምና ታሪክ ተመዘገበ
15:36 24.01.2026 (የተሻሻለ: 15:44 24.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተቆረጠ የብልት ክፍልን በረቀቀ የቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ በመቀጠል አዲስ የሕክምና ታሪክ ተመዘገበ
የአለርት ኮሞፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዶክተሮች አደጋ ከደረሰበት 9 ሰዓት ያለፈውን ወጣት ብልት ለማዳን የነበረውን ጠባብ ግዜ በአግባቡ በመጠቀም ሕክምናውን እንዳከናወኑ ተገልጿል፡፡
⏰ 6 ሰዓታትን በፈጀው አስቸኳይ የቀዶ ጥገና የሽንት ቱቦው፣ የቆዳው እና ሌሎች የድጋፍ አካላቶችን ቅርጽ እና ተግባር ወደነበረበት መመለስ ተችሏል።
ሆስፒታሉ ተከላው ስኬታማ እንደነበር እና ታካሚው በጥሩ ሁኔታ እያገገመ እንደሚገኝ ገልጿል።
ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ረቂቅ የተከላ ቀዶ ጥገና ትልቅ እርምጃ እና በጣም ውስብስብ እና ጊዜ የሚወስዱ ጉዳቶች ሀገር ውስጥ በብቃት፣ በቡድን ሥራ እና በላቀ የቀዶ ጥገና ሊታከሙ እንደሚችሉ ያሳያ ነው ሲል አለርት ኮሞፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማኅበራዊ ገጹ አስፍሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X