የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ ስመጥር ዩኒቨርሲቲ የሩሲያ ቋንቋ ትምህርትን ግዴታ ሊያደርግ ነው
14:23 24.01.2026 (የተሻሻለ: 14:24 24.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ ስመጥር ዩኒቨርሲቲ የሩሲያ ቋንቋ ትምህርትን ግዴታ ሊያደርግ ነው
የኪንሻሳ ነፃ ዩኒቨርሲቲ በሩሲያ የፓትሪስ ሉሙምባ የሕዝባዊ ወዳጅነት ዩኒቨርሲቲ (ሩዲን) ድጋፍ፤ ለአዲሱ የግዴታ መርኃ-ግብር 280 የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ያቀፉ 14 የጥናት ቡድኖችን መስርቷል ሲሉ የሩዲን ዋና ኃላፊ ኦሌግ ያስትሬቦቭ ተናግረዋል።
ግንባር ቀደሙ የሩሲያ የዓለም አቀፍ ትምህርት ልውውጥ ዩኒቨርሲቲ ሩዲን፤ የትምህርት ፕሮግራሙን ለማስጀመር የመማሪያ መጽሐፍት እና መምህራንን እንደሚያቀርብ ያስትሬቦቭ አክለዋል።
"ይህ ከዘንድሮ ዓመት ቀዳሚ ደማቅ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን ከአፍሪካ ግዙፍ ሀገራት በአንዷ ትልቅ ተቋም ውስጥ የሩሲያ ቋንቋ ተነሳሽነትን ማስተዋወቅ በመቻላችን ኩራት ይሰማናል" ሲሉ በስፑትኒክ እናት ኩባንያ የሚዲያ ግሩፕ የፕሬስ ማዕከል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ሩዲን በዓለም አቀፍ የትብብር ማዕቀፍ ስር በዓለም ዙሪያ ከ120 በላይ የጋራ የትምህርት ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ያደርጋል። ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም የቀድሞ ተመራቂ ልጆች እና የልጅ ልጆች የሩሲያ ቋንቋን በበየነ መረብ እንዲማሩ ዕድል ያመቻቻል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X