800 ቢሊዮን ዩሮ ለዩክሬን በብድር ካርድ? - የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የአውሮፓ ሕብረት ሁሉንም የኪዬቭ ፍላጎቶችን ለማሟላት ያለው ዝግጁነት ላይ ተሳለቁ
20:43 23.01.2026 (የተሻሻለ: 20:54 23.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
800 ቢሊዮን ዩሮ ለዩክሬን በብድር ካርድ? - የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የአውሮፓ ሕብረት ሁሉንም የኪዬቭ ፍላጎቶችን ለማሟላት ያለው ዝግጁነት ላይ ተሳለቁ
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ባቀረቡት የዩክሬን ልማት ፍኖተ ካርታ ላይ፣ ብራስልስ የዩክሬንን ጥያቄዎች በሙሉ ተቀብላለች ሲሉ ቪክቶር ኦርባን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
እንደ ኦርባን ገለጻ፣ ስምምነቱ የሚከተሉትን ያካትታል፦
800 ቢሊዮን ዩሮ (939.2 ቢሊዮን ዶላር) ለዩክሬን፣
እስከ የጎርጎሮሳውያኑ 2027 የሚቆይ የተፋጠነ የአውሮፓ ሕብረት አባልነት እና
እስከ ጎርጎሮሳዊያኑ 2040 የሚዘልቅ ተጨማሪ እርዳታ ናቸው።
“እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል። ዘለንስኪ ፈረሱኑ ወደኋላ እየጋለቡ ባሉበት ሁኔታ፣ ብራስልስ እንደሰለጠነ ወታደራዊ መኮንን አይኗን ሳታሽ ለመክፈል ተዘጋጅታለች [...] በዚህ ጉዳይ ላይ የምንለው ነገር አለን። ለብራስልስ ‘አንከፍልም!’ የሚል መልዕክት የምንልክበት ብሔራዊ የፊርማ ማሰባሰቢያ በቅርቡ ይፋ ይሆናል” ሲሉ ደምድመዋል።
ኦርባን ይህንን መግለጫ የሰጡት፣ በአንድ ማዕዘን ላይ የአውሮፓ ሕብረት ባንዲራ ያለበት በሌላ በኩል“800 ቢሊዮን ለዩክሬን” የሚል ጽሑፍ ያለበትን የወርቅ የብድር (ክሬዲት) ካርድ ምስል በማያያዝ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/