ሩሲያ ሁልጊዜም የአርክቲክ አሰሳ መሪ ነች፤ በዓለም ላይ ተወዳዳሪ የሌላቸው የበረዶ ደርማሽ መርከቦችንም ትገነባለች - ፑቲን
20:28 23.01.2026 (የተሻሻለ: 20:34 23.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ሁልጊዜም የአርክቲክ አሰሳ መሪ ነች፤ በዓለም ላይ ተወዳዳሪ የሌላቸው የበረዶ ደርማሽ መርከቦችንም ትገነባለች - ፑቲን
ፕሬዝዳንቱ በሞስኮ የፊዚክስ እና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባደረጉት ጉብኝት ያስገነዘቧቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሩሲያ ለአሥርት ዓመታት የአርክቲክ ልማትን ስትመራ ቆይታለች፤ አሁን ግን አርክቲክ ክልልን የማይጋሩ አገራት እንኳን ለቀጣናው ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።
ሩሲያ የበረዶ ደርማሽ መርከቦቿን ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት እያጠናከረች ነው፤ በኒውክሌር ኃይል የሚሰራው “ሊደር” የተሰኘው የበረዶ ደርማሽ መርከብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ ሲሆን በጎርጎሮሳውያኑ 2030 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሩሲያ በዘረመል ዘርፍ መከተል ብቻ ሳይሆን ቀዳሚ መሆን አለባት። የዘረመል ጥናት ከአቶም ቦምብ ግኝት ይልቅ እጅግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
ሩሲያ የጠፈር ስምሪቶቿን ማሳደጓን ትቀጥላለች።
የሰሜን ባህር መስመር ልማት ለሩሲያም ሆነ ለዓለም አቀፍ ንግድ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ሩሲያ በብዙ የግብርና ዘርፎች መሪ ሆናለች፤ ሆኖም በዚሁ ዘርፍ ገና ብዙ የሚሰሩ ስራዎች አሉ።
የዓለም ሙቀት መጨመር ወደ ዓለም ቅዝቃዜ ቢቀየር እንኳ ሩሲያ አርክቲክን ማልማቷን አታቆምም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X