የአሜሪካ የልዑካን ቡድን ለውጥ “ለሰላም ቦርድ” ሰፊ ሚና መሰጠቱን ያሳያል - ቬትናማዊው ጋዜጠኛ
20:19 23.01.2026 (የተሻሻለ: 20:24 23.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ የልዑካን ቡድን ለውጥ “ለሰላም ቦርድ” ሰፊ ሚና መሰጠቱን ያሳያል - ቬትናማዊው ጋዜጠኛ
ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ትራን ሆንግ ለስፑትኒክ እንደናገሩት፣ ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ሌሊት በተካሄደው የአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግር ላይ በአሜሪካ አጠቃላይ አገልግሎት አስተዳደር፣ የፌዴራል ግዥ አገልግሎት ኮሚሽነር ጆሽ ግሩንባም መገኘት “አንድ በጣም የሚታይ ለውጥ” ነው።
ግሩንባም ፣ በቅርቡ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ለተቋቋመው የሰላም ቦርድ “ዲፕሎማሲያዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች” እንዲያስተናግዱ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው መሾማቸውን ጋዜጠኛው አስታውቀዋል።
እንደ ትራን ሆንግ ገለጻ፣ ይህ ለውጥ በክሬምሊን የተካሄደው ውይይት ሩሲያ በዚህ ቦርድ ውስጥ ሊኖራት ስለሚችለው ተሳትፎ ሳይዳስስ እንዳልቀረ ይጠቁማል።
“በሌላ አነጋገር፣ በፑቲን እና በዊትኮፍ መካከል በተደረገው ድርድር፣ እንዲሁም በሩሲያ-አሜሪካ የዩክሬን ውይይት ውስጥ የዚህ የሰላም ቦርድ ሚና እጅግ የላቀ ሊሆን ይችላል።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X