የአየር ኃይልን 90ኛ ዓመት በማስመልከት የድሮን ትርዒት ተካሄደ
20:05 23.01.2026 (የተሻሻለ: 20:14 23.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአየር ኃይልን 90ኛ ዓመት በማስመልከት የድሮን ትርዒት ተካሄደ
ትርዒቱ የአየር ኃይሉን የሚወክሉ ልዩ ልዩ ምስሎች ታይተውበታል፡፡ ከዚህ ባሻገር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምሥልም ቀርቦበታል፡፡
አመሻሹን የተካሄደው ይህ ትርኢት በአባታቸው ሩሲያዊ በእናታቸው ኢትዮጵያዊት የነበሩት ሻለቃ ሚሽካ ባቢቼፍንም ዘክሯል፡፡
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሻለቃ ሚሽካ ባቢቼፍን ሕዳር 20 ቀን 1928 ዓ/ም የአየር ኃይል አዛዥ አድርገው በመሾም የአፍሪካ የመጀመሪያውን አየር ኃይል ምሥረታን አብሥረዋል፡፡
ይህ ቀን የአየር ኃይሉ ትክክለኛ የምሥረታ ዕለት መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X








