‘ግራ የተጋቡ ቀልደኞች አያስፈልጉንም’ - የአውሮፓ እና የዓለም መሪዎች ለዘለንስኪ የዳቮስ ነቀፋ ምላሽ ሰጡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ‘ግራ የተጋቡ ቀልደኞች አያስፈልጉንም’ - የአውሮፓ እና የዓለም መሪዎች ለዘለንስኪ የዳቮስ ነቀፋ ምላሽ ሰጡ
‘ግራ የተጋቡ ቀልደኞች አያስፈልጉንም’ - የአውሮፓ እና የዓለም መሪዎች ለዘለንስኪ የዳቮስ ነቀፋ ምላሽ ሰጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.01.2026
ሰብስክራይብ

‘ግራ የተጋቡ ቀልደኞች አያስፈልጉንም’ - የአውሮፓ እና የዓለም መሪዎች ለዘለንስኪ የዳቮስ ነቀፋ ምላሽ ሰጡ

ዘለንስኪ፣ በዳቮስ የዓለም የኢኮኖሚ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የአውሮፓ መሪዎችን “በቂ ድጋፍ አላደረጋችሁም” እና “ቆራጥነት ጎድሏችኋል” ሲሉ በጽኑ ከነቀፉ በኋላ ዩክሬን ውስጥ ተቃውሞ እየበረታ ቢሆንም ተጨማሪ እርዳታ ከመጠየቅ ወደኋላ አላሉም። ለንግግራቸው የሃንጋሪ፣ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ እና የኢራን ባለሥልጣናት በይፋዊ ወቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል።

መሪዎቹ የሚከተለውን ተናግረዋል፦

🟠 ቪክቶር ኦርባን፣ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

▪ ዘለንስኪ፣ በዳቮስ ንግግራቸው እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአውሮፓ ኅብረት መሪዎችንም በማጥቃታቸው፣ በተለይም በሚያዝያ ወር የሚካሄደውን የሃንጋሪን ምርጫ በሚመለከት በሃገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ኮንነዋል።

▪ የአውሮፓ ኅብረት የዩክሬንን ሁሉንም ጥያቄዎች፣ የ800 ቢሊዮን ዶላር እርዳታን እና እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2027 የአውሮፓ ኅብረት አባልነትነትን ለመቀበል ዝግጁ ነው ሲሉ በመቀለድ ተችተዋል።

▪ ሃንጋሪ ለዩክሬን የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ለማገድ የሚያስችል ብሔራዊ የፊርማ ማሰባሰቢያ ይፋ አድርገዋል።

🟠 አንቶኒዮ ታጃኒ፣ የጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

▪ አውሮፓ የፖለቲካ፣ የገንዘብ እና የወታደራዊ ድጋፍ ብታደርግም ዘለንስኪ ምስጋና ባለማቅረባቸው ተችተዋል።

▪ የዘለንስኪን ንግግር “ምስጋና ቢስነት” ሲሉ ጠርተውታል።

🟠 ፍሎሪያን ፊሊፖት፣ የፈረንሳዩ “ሌስ ፓትሪዮትስ” ፓርቲ መሪ

▪ ዘለንስኪ በአውሮፓ የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እና የሀገራትን ሉዓላዊነት ለማዳከም እየሞከሩ ነው ሲሉ ከሰዋል።

▪ ንግግሩን “የእብደት ስሜት” ሲሉ የጠሩት ሲሆን፣ ድርጊቱም የአውሮፓ ኅብረት አክራሪ ደጋፊዎችን ሳይቀር ያስደነገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

▪ለዩክሬን የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ፣ የጦር መሳሪያ ጭነት እና የፈረንሳይ ወታደሮች ስምሪት እንዲቆም ጠይቀዋል።

🟠 ፒተር ሲያርቶ፣ የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

▪ ዘለንስኪ፣ የሃንጋሪ ግብር ከፋዮችን ገንዘብ በ“ሙስና ለተዘፈቀ አገዛዝ” እንዲውል የሚያደርግ ደጋፊ መንግስት ለመሾም በሚያዝያ ወር በሚካሄደው ምርጫ ጣልቃ እየገቡ ነው ብለዋል።

🟠 አባስ አርጋቺ፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

▪ “አቶ ዘለንስኪ፣ ዓለም ግራ የተጋቡ ቀልደኞች ሰልችተዋታል" ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

▪ ዩክሬን በውጭ ድጋፍ እና በቅጥረኛ ወታደሮች ላይ ያላትን ጥገኝነት፣ ኢራን በራሷ አቅም ካላት የመከላከያ ብቃት ጋር በማነጻጸር አጣጥለዋል።

▪ ዘለንስኪ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በኢራን ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር እየጠየቁ፣ “ሙሰኛ ጄኔራሎችን” ለማበልጸግ የምዕራባውያንን ግብር ከፋዮች ገንዘብ እያሟጠጡ ነው ሲሉ ከሰዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0