ተርስድ የኢትዮጵያን አበቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የአንድ ዓመት የትብብር ሥራ መጀመሩን አስታወቀ
18:50 23.01.2026 (የተሻሻለ: 19:04 23.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ተርስድ የኢትዮጵያን አበቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የአንድ ዓመት የትብብር ሥራ መጀመሩን አስታወቀ
በአበባ እና ተክሎች ኢንዱስትሪ የዓለም ዋንኛ የዲጂታል መድረክ የሆነው ተርሰድ፣ ከኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር ጋር ያደረገው የዝግጅት (ኤዲቶሪያል) ትብብር፣ የኢትዮጵያ አበቦች በዓለም ዙሪያ ባሉ ገዢዎች፣ የአበባ ነጋዴዎች እና በአጠቃላይ በአበባ አፍቃሪዎች ዘንድ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ገጽታ ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው።
መርሃ ግብሩ፣ ኢትዮጵያ የአበባ መገኛ መሆኗን በተከታታይ እና በታማኝ ትርክቶችን በመገንባት፣ የገዢዎችን እምነት ለማጠናከር ያግዛል ተብሏል።
በተጨባጭ ማስረጃዎች እና በዓለም አቀፍ የሆርቲካልቸር የሚዲያ መስመሮች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ሀገሪቱ በዘርፉ ያላትን ጠቀሜታ ማሳየት ማለሙንም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

