አሜሪካ ግሪንላንድን 'እየጠበቀች' እንደመሆኗ የደሴቷን የማዕድን ሀብት ትሻለች - ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ

ሰብስክራይብ

አሜሪካ ግሪንላንድን 'እየጠበቀች' እንደመሆኗ የደሴቷን የማዕድን ሀብት ትሻለች - ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ

​"በመሰረቱ እኛ እየጠበቅነው ባለው በዚህ እጅግ ብዙ ማዕድናት እና የተፈጥሮ ሀብቶች ባሉት ውብ ምድር፣ ከሀብቱ ተቋዳሽ መሆን እንፈልጋለን፣" ሲሉ ጄዲ ቫንስ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

​ የቫንስ መግለጫ፣ ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውድቅ ካደረጉት "ለዋሽንግተን የግሪንላንድ አስፈላጊነት በሀብት ላይ የተመሰረተ ነው" ከሚለው ሃሳብ ለውጥ መኖሩን ያሳያል።

​ባለፈው ረቡዕ በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ትራምፕ ሲናገሩ፣ በዴንማርክ ግዛት ስር ራስ ገዝ ከሆነችው ግሪንላንድ ጋር በተያያዘ ከኔቶ አባሏ ዴንማርክ ጋር ጦርነት ውስጥ ይገባሉ ተብሎ እንደማይጠበቅ ግልጽ አድርገዋል።

​ከኔቶ ባለስልጣናት ጋር ከተደረጉ ንግግሮች በኋላ የስምምነት መሰረት እየተገነባ መሆኑን የጠቀሱት ትራምፕ፣ ስለ ደሴቱ የረጅም ጊዜ ወይም "ዘላለማዊ" ስምምነት እየተወያዩ መሆኑን ገልጸዋል።

​ የዴንማርክ እና የግሪንላንድ ባለስልጣናት ደሴቲቱ የአሜሪካ አካል መሆን አለባት የሚለውን የትራምፕን ሃሳብ በመቃወም፣ አሜሪካ የግዛት አንድነታቸውን እንድታከበር በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0