የሳሕል ጥምረት አገራት ባንክ - ለሳሕል አገራት ሉዓላዊነት ‘ታሪካዊ’ እርምጃ ነው - ኢኮኖሚስት
16:36 23.01.2026 (የተሻሻለ: 16:44 23.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሳሕል ጥምረት አገራት ባንክ - ለሳሕል አገራት ሉዓላዊነት ‘ታሪካዊ’ እርምጃ ነው - ኢኮኖሚስት
የኮንፌዴራል የኢንቨስትመንት እና ልማት ባንክ መቋቋም፣ ብድር ለመስጠት ቅድመ ሁኔታዎችን ከሚያስቀምጡ እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ካሉ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት “የሚበጥስ” መሆኑን መሐመድ ዲያኪቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
“ይህ ውሳኔ የሳሕል አገራት ጥምረት፣ አባል አገራት በራሳቸው የነደፉትን ሉዓላዊ የፋይናንስ መሣሪያ ለመታጠቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል። በተጨማሪም ከ70 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላቸውን እና በማዕድን፣ በግብርና እንዲሁም በኢነርጂ ሀብት የበለጸጉትን እነዚህን ሦስት አገራት በኢኮኖሚ ለማቀናጀት የሚያገለግል መሣሪያ ነው ብለዋል።”
ምን ይለወጣል? እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ ባንኩ ትርፍ ለማግኘት ብቻ ሳይሆን “ከሳሕል ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ” እና መዋቅራዊ ፕሮጀክቶችን የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚችል ይሆናል።
ባለሙያው የሚከተሉትን ዘርፎች እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል፦
ኃይል
ትራንስፖርት
አግሮ-ኢንዱስትሪ
የሀገር ውስጥ ምርት ማቀነባበሪያ
ተጨማሪ እሴት የሚፈጥሩ የማዕድን ፕሮጀክቶች እና
መሠረታዊ የመድኃኒት ኢንዱስትሪ።
“የሳሕል ጥምረት አገራት ባንክ ስጋቶችን በመቀነስ፣ የጋራ ፋይናንስን በማሰባሰብ እና ኢንቨስትመንቶችን ወደ አገር ውስጥ ሀብት ማቀነባበሪያ እና ቀጣናዊ ኢኮኖሚ ትስስር እንዲመሩ በማድረግ ረገድ አነቃቂ ሚና ሊጫወት ይችላል” ሲሉ መሐመድ ዲያኪቴ ደምድመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X