ኢትዮጵያ እና ቤላሩስ በወታደራዊ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ
15:55 23.01.2026 (የተሻሻለ: 16:04 23.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቤላሩስ በወታደራዊ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ
ስምምነቱን፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ እና የቤላሩስ አቻቸው ዲምትሪ ፓንተስ ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ስምምነቱ የኢትዮጵያን ወታደራዊ ቴክኖሎጂና ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እንዲሁም በወታደራዊ ምርቶች ራሳችንን ለመቻል እየተደረገ ላለው ጥረት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
ይህ ስምምነት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የተፈራረሙትን ስትራቴጂካዊ ስምምነት ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፣ ሁለቱ ሀገራት የነበራቸውን የረጅም ጊዜ ወዳጅነትን የሚያጠናክር እንደሆነም ተናግረዋል።
የቤላሩሱ ሚኒስትር በበኩላቸው፣ ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ የጠቆሙ ሲሆን፣ ስምምነቱ በተለያዩ አዳዲስ ዘርፎች ለመሰማራት የሚያስችል ዕድል የፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል።
የቤላሩስ አየር ኃይል ከነገ ጀምሮ በሚከበረው 90ኛው የኢትዮጵያ የአየር ኃይል የምሥረታ በዓል ላይ የአየር ትርኢት እንደሚያቀርብና ልዑካኑም እንደሚታደሙ መከላከል ሚኒስቴር በማኅበራዊ የትስስር ገፁ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X