በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል ለተፈረመው ዘላቂ የሰላም ስምምነት፣ የማስፈፀሚያ ውል ተፈረመ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል ለተፈረመው ዘላቂ የሰላም ስምምነት፣ የማስፈፀሚያ ውል ተፈረመ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል ለተፈረመው ዘላቂ የሰላም ስምምነት፣ የማስፈፀሚያ ውል ተፈረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.01.2026
ሰብስክራይብ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል ለተፈረመው ዘላቂ የሰላም ስምምነት፣ የማስፈፀሚያ ውል ተፈረመ

ኅዳር 25፥ 2018 ዓ.ም በሁለቱ ወገኖች መሃከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት ማሰፈፀሚያ ነጥቦች ያሉትን አዲሱን ስምምነት፣ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ እና የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኢያሱ አባተ ተፈራርመዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ መሀመድ እድሪስ፣ በክልሉ የነበረው ግጭት ከፍተኛ ውድመትን ያስከተለ መሆኑን እና ህዝቡ ሊያገኝ የሚገባውን የሰላምና የልማት ያሉ ሰብአዊ መብቶችን ማጣቱን  ገልፀዋል።

አክለውም፣ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ከሰላም ይልቅ አፈ ሙዝ ይዞ መፉተግ ጊዜውን የማይመጥን እና በትውልድ ተወቃሽ የሚያደርግ ነው ሲሉ ሰላምን የመረጡትን በማመስገን ቀሪ ኃይሎች የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአፋሕድ ከፍተኛ አመራር ኮለኔል ፈንታው ሙሀባ በበኩላቸው፣ “ባለፈው ጦርነት የአማራ ሕዝብ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የዐይን እማኝ ነን፤ ክልሉም ከዚህ በላይ ጦርነት የመሸከም አቅም የለውም” ሲሉ መናገራችወን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገበዋል፡፡

በስምምነት መድረኩ የክልሉ የመንግስት አመራሮች፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች እንዲሁም በመንግስት የቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የአፋህድ ከፍተኛ አመራሮች  ተገኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0