የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት ስድስት ወራት ከ445 ኪሎ ግራም በላይ አደገኛ ዕፅዋት ከነአዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ማዋሉን አስታወቀ
18:59 22.01.2026 (የተሻሻለ: 19:04 22.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት ስድስት ወራት ከ445 ኪሎ ግራም በላይ አደገኛ ዕፅዋት ከነአዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ማዋሉን አስታወቀ
ይህም መጠን ከ2017 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር፣ መጠኑ መቀነሱ የቁጥጥር ሂደቱ ዘመናዊ አሠራር የተከተለ እና ውጤታማ መሆኑን ያሳያል ሲል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በተካሄደው የአደገኛ ዕፅዋት ቁጥጥር ስራዎች፣ ኮኬይንና ካናቢስ የተባሉ አደገኛ ዕፆች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና በተከናወነው ጠንካራ የፍተሻና የክትትል ሥራዎች የ13 ሀገራት ዜግነት ያላቸው 19 ግለሰቦች በዝውውሩ ሲሳተፉ መያዛቸውን ተገልጿል።
በቀጣይም አደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአዘዋዋሪዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ አሳውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X