በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ5.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ5
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ5 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.01.2026
ሰብስክራይብ

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ5.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

ገቢው፣ ሀገሪቷ በግማሽ ዓመቱ አገኘዋለሁ ብላ ካቀደችው 4.42 ቢሊዮን ዶላር በላይ በመሆን የዕቅዱን 120 በመቶ አሳክቷል ሲሉ ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ገልፀዋል።

የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ1.83 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ይህም በውጭ ንግድ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ እድገት መታየቱን ያንፀባርቃል ብለዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

መንግሥት እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 9.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የያዘውን አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ግብ ለማሳካት በትኩረትና በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0