ትራምፕ የታልቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ዳግም ለማሸማገል እንደሚጥሩ ቃል ገቡ

ትራምፕ የታልቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ዳግም ለማሸማገል እንደሚጥሩ ቃል ገቡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን የቆየ ውዝግብ ለመፍታት የአሜሪካን ጥረት ለማደስ ቃል ገብተዋል፡፡ ጉዳዩን "በጣም አደገኛ" ሲሉ የገለጹት ቢሆንም ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ትራምፕ በግድቡ የናይል ውሃ ክፍፍል ላይ ያለውን ውጥረት ለመፍታት የግብፁን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ እና የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በማቀራረብ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።
ትራምፕ በአንደኛ የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካ "ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርባ እንደነበር" ገልጸው፣ የግብፅን በናይል ላይ ያላትን ታሪካዊ ጥገኝነት በማጉላት "ጉዳዩን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስ" ቃል ገብተዋል።
🟠 የሦስቱ አገራት አቋም ምንድን ነው?
ግብፅ፦ የውሃ ድርሻዋ መቀነሱን እና በድርቅ ዓመታት የውሃ ፍሰትን እንደሚቀንስ በመጥቅስ አስገዳጅ ስምምነት እንድትደረግ ትጠይቃለች።
ሱዳን፦ ለርካሽ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እና ቁጥጥር ለሚደረግበት የውሃ ፍሰት የምትደግፍ ቢሆንም፣ ፍትሐዊ ጥቅሞች እና ደህንንነትን የሚያረጋግጥ የሦስትዮሽ ማዕቀፍ ትሻለች፡፡
ኢትዮጵያ፦ የኃይል ማመንጫው ለዜጎቿ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እና ለልማት አስፈላጊ የሆነ የሉዓላዊነት ፕሮጀክት ከመሆኑ ባሻገር ለታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት ጠቃሚ መሆኑን ትሞግታለች፡፡ በአባይ ውሃ አጠቃቀም መብቷ ላይ የሚጣሉ ገደቦችንም ትቃወማለች። ግብፅና ሱዳን ያላፀደቁትና 7 የተፋሰሱ አገራት ያፀደቁት የናይል ወንዝ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ትሻለች፡፡
የሀገራቱ መሠረታዊ አለመግባባት ቀደም ሲል የግድቡን የውሃ ሙሌት የነበረ ሲሆን፣ አሁን ላይ የውሃው ፍሰት፣ አስተዳደር እና የውሃ ክፍፍል ስምምነት በተመለከተ ሰፊ የቋም ልዩነቶች መኖራቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ የቀኝ ግዛት ውል ስትል ውድቅ ያደረገችው የ1959ኙ የግብፅ እና ሱዳን የውሃ ድርሻ ስምምነት ሌላኛው ያለመስማማታቸው ምክንያት ነው።
ሦስቱ አገራት በውሃ ክፍፍል ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከደርዘን ጊዜ በላይ ድርድር ቢያደርጉም ጥረታቸው እስካሁን ፍሬ አላፈራም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X