ኢትዮጵያ ከሦስት የብሪክስ አባላት ጋር ፍርደኞችን የማስተላለፍና የወንጀል ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠት አዋጆችን አፀደቀች
17:27 22.01.2026 (የተሻሻለ: 17:34 22.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከሦስት የብሪክስ አባላት ጋር ፍርደኞችን የማስተላለፍና የወንጀል ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠት አዋጆችን አፀደቀች
አዋጆቹን ያፀደቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነት ከቻይና እና ከብራዚል መንግሥታት ጋር የተደረገ መሆኑን አስታውቋል።
በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን የአሳልፎ የመስጠት ስምምነቱ ደግሞ በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ መንግሥታት መካከል የተደረገ ነው፡፡
በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው ዜጎቻቸን፣ ፍርዳቸውን በሀገራቸው ጨርሰው እና ታርመው ወደ ማኅበረሰባቸው እንዲቀላቀሉ የሚያግዝ አዋጅ መሆኑን በምክር ቤቱ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

