የካናዳ ጦር በአሜሪካ ሊፈፀም ለሚችል መላምታዊ ወረራ የሽምቅ ውጊያ ስልቶች ላይ እተዘጋጀ መሆኑ ተዘገበ

የካናዳ ጦር በአሜሪካ ሊፈፀም ለሚችል መላምታዊ ወረራ የሽምቅ ውጊያ ስልቶች ላይ እተዘጋጀ መሆኑ ተዘገበ
ባለፉት መቶ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የካናዳ ጦር ኃይል ከአሜሪካ ሊሰነዘር ለሚችል ጥቃት ሊሰጥ የሚችለውን ምላሽ "በሲሙሌሽን" (የእውነተኛ ዉጊያ አምሳል) ማዘጋጀቱን ሁለት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የጠቀሱ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
በዚህ ሁኔታ ጦሩ ጥቃቱ ከደቡብ አቅጣጫ ሊመጣ እንደሚችል ይገምታል፤ የአሜሪካ ጦር ቁልፍ የሆኑ የካናዳ ስልታዊ የየብስ እና የባህር ይዞታዎችን ከሁለት ቀናት ባነሰ ወይም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከጥቅም ውጭ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ታስቧል።
የካናዳ መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን ወረራ ለመመከት የሚያስችል የተለመደ የጦር መሣሪያ አቅም እንደሌላት አምናለች። በመሆኑም የታቀደው ምላሽ በአፍጋኒስታን ሙጃሂዲኖች ስልት ላይ የተመሠረተ የሽምቅ ውጊያ፣ አድብቶ ማጥቃት፣ ማውደም እና የድሮን ጥቃቶችን የሚጠቀም ይሆናል።
ይህ "የሲሙሌሽን" ልምምድ ለመረጃ ያህል ብቻ የተደረገ ሲሆን፣ የካናዳ መሪዎች የአሜሪካ ወረራ የመፈጸም ዕድል እጅግ በጣም አነስተኛ መሆኑን እንደሚያምኑ ሚዲያው ጠቅሷል።
ምንም እንኳን የባለሥልጣናቱ እንደዛ ቢያምኑም፣ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን በታህሳስ ወር መጨረሻ እንደዘገቡት፣ አንዳንድ ካናዳውያን ከቬንዙዌላ ቀጥሎ የትራምፕ ቀጣይ ኢላማ እንሆናለን የሚል ስጋት አላቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X