በዳቮስ ሊፈረም የነበረው የዩክሬን መልሶ ግንባታ ዕቅድ መራዘሙን ዘገባዎች አመላከቱ
18:47 21.01.2026 (የተሻሻለ: 18:54 21.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዳቮስ ሊፈረም የነበረው የዩክሬን መልሶ ግንባታ ዕቅድ መራዘሙን ዘገባዎች አመላከቱ
በዩክሬን፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ መካከል ስምምነት ሊደረግበት የነበረው የ800 ቢሊዮን ዶላር የብልጽግና ዕቅድ፣ በዚህ ሳምንት በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ነገር ግን ፊርማው መራዘሙን የምዕራባውያን ስድስት ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
መራዘሙ በዋሽንግተን እና በአውሮፓ ሀገራት መካከል በግሪንላንድ ጉዳይ እና በትራምፕ በኩል በቀረበው የጋዛ የሰላም ምክር ቤት ዙሪያ በተፈጠረ ከፍተኛ አለመግባባት ምክንያት መሆኑን ሚዲያው ጠቁሟል።
ለዩክሬን የሚደረገው የድህረ-ጦርነት የኢኮኖሚ ድጋፍ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አልተደረገም፤ በቀጣይ ቀናትም ሊፈረም እንደሚችል ሚዲያው አክሏል።
ዘለንስኪ በትናትናው ዕለት ወደ ዳቮስ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ የሰረዙ ሲሆን፣ ወደ ጉባኤው የሚሄዱት ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው የደህንነት ዋስትና ሰነድ እና የብልጽግና ዕቅዱ ለፊርማ ዝግጁ ሲሆኑ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X