ኢትዮጵያ በዳቮስ የ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለንግድና ለጤና ማሻሻያዎች ጥሪ አቀረበች
16:50 21.01.2026 (የተሻሻለ: 16:54 21.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዳቮስ የ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለንግድና ለጤና ማሻሻያዎች ጥሪ አቀረበች
በዓመታዊው ስብሰባ ላይ ከፍተኛ ልዑካን ቡድንን በመምራት በስፍራው የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ፣ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ለአኅጉሪቱ ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንዳለው በመድረኩ ላይ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም፣ የ2026ቱ "ለሥራ ዕድል ቅድሚያ የሚሰጥ የነፃ የንግድ ቀጣና የምርት ስምምነት" የሥራ ዕድልን ለማስፋፋት እንዲሁም ወጣትና ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት ወሳኝ ማዕቀፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
"አዲሱ ዓለም አቀፍ ጤና መዋቅር" በሚል በተካሄደው ውይይት ላይ ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና በአገራት መሪነት የሚመራ ዓለም አቀፍ የጤና ፋይናንስ ሥርዓት እንዲኖር ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ለሉሳካ አጀንዳ እና "አንድ ዕቅድ፣ አንድ በጀት፣ አንድ ሪፖርት" ለሚለው መርህ ቁርጠኛ መሆኗንና በዓለም አቀፍ ጤና ረገድ ፍትሐዊነት፣ አንድነት እና የጋራ ኃላፊነት እንዲሰፍን አሳስበዋል" ሲል ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X