ቦይንግ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘጠኝ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ግዢ ስምምነትን ይፋ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቦይንግ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘጠኝ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ግዢ ስምምነትን ይፋ አደረጉ
ቦይንግ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘጠኝ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ግዢ ስምምነትን ይፋ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.01.2026
ሰብስክራይብ

ቦይንግ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘጠኝ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ግዢ ስምምነትን ይፋ አደረጉ

የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የረጅም ርቀት በረራ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ አውሮፕላኖቹ መታዘዛቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

"ይህ ትዕዛዝ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በረራዎቻችንን ለማሻሻል ያለንን ቀጣይ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፣ በዚህም የደንበኞች አገልግሎት የበለጠ ያጠናክራል" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

145 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ትልቁን የ787 ድሪምላይነር ስብስብ የሚያንቀሳቅስ ሲሆን፣ የ787-8 እና 787-9 ጄቶቹን ወደ አውሮፓ፣ እስያ እና ሰሜን አሜሪካ እንዲሁም ከፍተኛ ፍላጎት ባለባቸው የአፍሪካ መስመሮች ላይ ያሰማራል ሲሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0