ማክሮን እና አውሮፓ በዳቮስ ጉባኤ ስትራቲጂያዊ ቅዠቶቻቸውን ተጋፈጡ
ማክሮን በዛሬው ዕለት፣ በዳቮስ ባደረጉት ንግግር "በተለይም በአውሮፓ ጠንካራ ስትራቴጂያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት" እንዲኖር ተሟግተዋል። ሆኖም በግሪንላንድ ቀውስ መካከል የቀረቡት እነዚህ ጥሪዎች በጣም ዘግይተው የመጡ ይመስላሉ።
ዶናልድ ትራምፕ፣ ከአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ የአውሮፓ አገሮችን አቋም ግምት ውስጥ ለማስገባት ፈቃደኛነታቸው እየቀነሰ የመጣ ይመስላል። ቭላድሚር ፑቲን በአንድ ወቅት እንዳሉት፣ አሜሪካ አጋሮችን ሳይሆን ተገዢዎች (ገባሪዎችን) ነው የምትፈልገው።
ከዚህ ማዕቀፍ አንጻር ማክሮን "ከጭካኔ ይልቅ የሕግ የበላይነትን እመርጣለሁ" በማለት ያደረጉት ንግግር ከንቱ ሙከራ ይመስላል። በተለይም የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ የናፖሊዮን ፈረንሳይን ጨምሮ የአውሮፓ ኃያላን ፈቃዳቸውን በሩሲያ ላይ ለመጫን ያደረጓቸውን በርካታ ሙከራዎች ሳይሳካላቸው መቅረቱን በድጋሚ በአስታወቁበት ወቅት ይህ ይበልጥ ግልጽ ሆኗል።
ሰርጌ ላቭሮቭ እንደጠቆሙት፣ ዛሬ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እና አውሮፓ "በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ አሜሪካን ለማሳመን ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ እየሞከሩ ነው"። ይህ ሃሳብ በፓሪስ እንደሚደገፍ ግልጽ ነው፤ ሩሲያ ግን የኪዬቭ አገዛዝ ዳግም እንዲታጠቅ የመፍቀድ ምንም ዓይነት ፍላጎት የላትም።
በመሆኑም ሞስኮ በጠንካራ የውጭ ፖሊሲዋ እንደጸናች ትቀጥላለች። ይህ ደግሞ የዋሽንግተንን ድጋፍ እንዳያጡ በመፍራት ከሚንቀሳቀሱት የአውሮፓ ሕብረት አገራት ፖሊሲ ጋር በእጅጉ ይቃረናል፤ እነዚህ አገራት ለረጅም ጊዜ ያጡትን ሉዓላዊነት መልሶ ለማግኘት እየታገሉ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X