ሞሮኮ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የፍፃሜ ጨዋታን በተመለከተ ክስ ልታቀርብ ነው
18:23 20.01.2026 (የተሻሻለ: 18:24 20.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሞሮኮ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የፍፃሜ ጨዋታን በተመለከተ ክስ ልታቀርብ ነው
ሞሮኮ በራባት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ፣ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በመጨረሻ ደቂቃ የተሰጣትን የፍጹም ቅጣት ምት ባታስቆትርም፣ በጭማሪ ሠዓት በሴኔጋል 1 ለ 0 ተሸንፋ ዋንጫውን ማጣቷ የሚታወስ ነው።
የጨዋታዉ የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (ቫር)፣ የሞሮኮው አጥቂ ብራሂም ዲያዝ ከትከሻው ተጎትቷል በሚል ምክንያት ለሞሮኮ የፍጹም ቅጣት ምት በመስተቱ፣ የሴኔጋል ተጫዋቾች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ከሜዳ ወጥተው ነበር፤ ዲያዝም የሴኔጋል ተጫዋቾች ወደ ሜዳ እስኪመለሱ ለ14 ደቂቃዎች ከጠበቀ በኋላ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
"ይህ ሁኔታ በጨዋታው መደበኛ ሂደት እና በተጫዋቾች ብቃት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል" ሲል የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
ሞሮኮ፣ ካቀረበችው የሕግ አቤቱታ ከጨዋታው ውጤት ተቃውሞ ባለፈ ምን ለማግኘት እንደፈለገች ግልጽ አይደለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X