ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለግብፅ እና ለሱዳን ካሳ መክፈል አለበት ሲሉ የግብፁ ሚኒስትር ተናገሩ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለግብፅ እና ለሱዳን ካሳ መክፈል አለበት ሲሉ የግብፁ ሚኒስትር ተናገሩ
የግብፅ የውሃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስትር ሀኒ ስዊለም፣ በአንድ ወገን እርምጃ የኢትዮጵያው የሚያህል ግድብ በናይል ወንዝ ላይ ተገንብቶ አያውቅም ብለዋል፡፡
በግድቡ ምክንያት 55 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የነበረው የግብፅ የውሃ ድርሻ 38 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ቀንሶ 17 ቢሊዮን ሜትር ኩብ መግባቱን በመጥቀስ የሀገራቸውን ጉዳት ለግብፅ ሴኔት አስረድተዋል። የግብፅ የውሃ ድርሻ 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ሀገሪቱ የውሃ ድርሻ ወደ 88.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ማሻቀቡንም ገልፀዋል፡፡
የግብጽ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ መግለጫዎች፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን በመጥቀስ "ታሪካዊ መብቶች" ላይ መተማመናችውን የሚያሳይ ነው ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ኮንኗል፡፡
“ከኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች የሚመነጨው አባይ ወንዝ፣ የናይል ተፋሰስን 86 በመቶ ውሃ ያዋጣዋል። የአባይ ተፋሰስ ውሃ የኢትዮጵያ 70 በመቶ የገጸ ምድር ውሃ ነው፤” ብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ግድቡ የተገነባው የጥቁር ሕዝብ ታሪክ ለመቀየር እንጂ በፍጹም ወንድሞቿን ለመጉዳት አለመሆኑን በግድቡ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ አረጋግጠዋል፡፡
ሱዳን በበኩሏ ግድቡን ለግብርና እና ለኤሌክትሪክ የሚሰጠውን ጥቅም ብታምንም፣ ከግድቡ የሚልቀቀው የማስተንፈሻ ውሃ የወንዝ ሙላትና የጎርፍ ማጥለቅለቅ አስከትሏል ስትክ ኢትዮጵያን ከስሳለች፡፡
በመስከረም ወር መጨረሻ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የሕዳሴ ግድብ የሱዳንን ጎርፍ ለመቀነስ መርዳቱን ጠቅሰው “ትርፍ ውሃ አልለቀቅንም” ብለዋል። ለሱዳን ጎርፍ ኢትዮጵያን ተጠያቂ የማድረግ የግብፅ ሀሰተኛ ውንጀላንም መሠረተ ቢስ መሆኑን ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X