በሕንድ 21ኛው የታታ ሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ ታዱ አባተ እና የሺ ካላዩ ድል ቀናቸው
17:26 20.01.2026 (የተሻሻለ: 17:34 20.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሕንድ 21ኛው የታታ ሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ ታዱ አባተ እና የሺ ካላዩ ድል ቀናቸው
ታዱ አባተ፣ ከኬንያው ሊዮናርድ ላንጋት እና ከኤርትራው መርሃዊ ከሰተ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ካደረገ በኋላ፤ የመጨረሻውን አንድ ኪሎ ሜትር ተነጥሎ በመውጣት ውድድሩን በ2፡09፡55 በማጠናቀቅ አሸንፏል።
በሴቶች በኩል የሺ ካላዩ፣ እጅግ ድንቅ ብቃት በማሳየት በዋና ዋና የማራቶን ውድድሮች የመጀመሪያዋን የድል ውጤት አስመዝግባለች፡፡ እስከ ውድድሩ ሦስት አራተኛ ድረስ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር በቡድን ስትሮጥ ቆይታ፣ በመጨረሻዎቹ ኪሎ ሜትሮች ብቻዋን በመገስገስ ውድድሩን በ2፡25፡13 አጠናቅቃለች።
⏲ የየሺ ውጤት በሙምባይ ማራቶን ታሪክ አምስተኛው ፈጣን የሴቶች ሠዓት ሆኖ መመዝገቡን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/