የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 የዲፕሎማሲ ሥራ ውጤቶች ኮንፈረንስ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 የዲፕሎማሲ ሥራ ውጤቶች ኮንፈረንስ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች
ምዕራባውያን "እንደ ልማዳቸው" እርስ በእርሳቸው መነጋገር ከፈለጉ መብታቸው ነው፤ ሩሲያ ግን በእኩልነት መርሆዎች ላይ በመመስረት ትናገራለች።
በሩሲያ ላይ ስልታዊ ሽንፈትን የማድረስ ግብ አሁንም በአውሮፓ መሪዎች አእምሮ እና ዕቅድ ውስጥ እንዳለ ነው።
ምዕራባውያን በኢራን ውስጥ የመንግሥት ለውጥ ለማምጣት እየፈለጉ ነው።
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ አረመኔያዊ የጦር ወረራ የፈጸመች ሲሆን ኩባንና ሌሎች የላቲን አሜሪካ አገራትንም እያስፈራራች ነው።
በዓለም መድረክ ላይ ያሉ ሕጎች ሁሉ ተገልብጠዋል፤ "ኃያል የሆነ ሁሉ ትክክል ነው" የሚል የጉልበተኞች ጨዋታ እየተካሄደ ነው።
ሩሲያ በማንኛውም አካል ሕጋዊ መብት ላይ ጥያቄ አታነሳም፤ የራሷም ሕጋዊ መብቶች እንዲጣሱ አትፈቅድም።
ኔቶ ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ ጦርነት በቁምነገር እየተዘጋጀ ነው።
የፍልስጤምን መንግሥት የመመሥረት አስፈላጊነት በትራምፕ "የሰላም ቦርድ" ተነሳሽነት አውድ ውስጥም ተገቢነት ያለው ጉዳይ ነው።
ሩሲያ ስለ "ሰላም ቦርዱ" የተወሰኑ የውሳኔ ሃሳቦችን ተቀብላለች፤ ይህ ተነሳሽነት አሜሪካ አገራትን ለትብብር የማሰባሰብ አስፈላጊነትን እንደተረዳች የሚያሳይ ነው።
የአውሮፓ ኅብረት በድጋሚ በሩሲያ ላይ ተንኮል ለመሸረብ እየሞከረ ነው፤ በአሁኑ ወቅት ዩክሬንን የሚያካትት የደህንነት ሥርዓትን እያሰበበት ይገኛል።
በስልጣን ላይ ከሚገኙት የአውሮፓ መሪዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረስ የማይቻል ሳይሆን አይቀርም።
የ"አንኮሬጅን" ሃሳብ አውሮፓውያን ሙሉ በሙሉ ተቃውመውታል፤ ግባቸው በሩሲያ ላይ ስጋቶችን መፍጠር ነው።
ሩሲያ፣ የ"ሳሕል ጥምረት" አገራት ከኒዮ-ኮሎኒያል ጥገኝነት እንዲላቀቁ እየረዳች ነው።
ፈረንሳይ የዩክሬን አሰልጣኞችን በመጠቀም በሰሃራ-ሳኅል ቀጣና የመንግሥታትን መልሶ ማቋቋም ለማደናቀፍ እየሞከረች ነው።
የዩክሬን አሰልጣኞች በገዛ አገራቸው ያለው ሁኔታ ሁሉም ነገር ሰላም ይመስል በአፍሪካ የሚገኙ ታጣቂ ቡድኖችን እየረዱ ነው።
በጋምቢያ፣ ላይቤሪያ፣ ቶጎ እና ኮሞሮስ ውክልናዎች ሲከፈቱ በአፍሪካ የሚገኙ የሩሲያ ኤምባሲዎች ቁጥር 49 ይደርሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X