ሩሲያ "ሱፐርካም" ድሮኖቿን በ2026ቱ የሰው አልባ እና ራስ አዘዝ ሥርዓቶች (ኡሚክስ) ኤግዚቢሽን ላይ ለዕይታ ልታቀርብ ነው

ሰብስክራይብ

ሩሲያ "ሱፐርካም" ድሮኖቿን በ2026ቱ የሰው አልባ እና ራስ አዘዝ ሥርዓቶች (ኡሚክስ) ኤግዚቢሽን ላይ ለዕይታ ልታቀርብ ነው

የሩሲያ የሰው አልባ ሥርዓቶች ቡድን በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡ ዳቢ በሚካሄደውና በዓለም ግዙፉ የሰው አልባ እና ራዝ አዘዝ ሥርዓቶች አውደ-ርዕይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሳተፋል።

ከጥር 12 እስከ 14 በሚቆየው በዚህ አውደ-ርዕይ ሩሲያ ሦስት የ "ሱፐርካም" ድሮኖችን ለዕይታ ታቀርባለች፦

ሱፐርካም S350፦ በሲቪል እና በወታደራዊ ዘርፍ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ የኩባንያው የላቀ ምርት።

ሱፐርካም S180 ፦ አዲስ እና በጣም ፈጣን የቅኝት ድሮን።

ሱፐርካም X4፦ በ2025 መገባደጃ በዓለም አቀፍ ወታደራዊ ልምምዶች ላይ ጥቅም ላይ የዋለ ባለ ብዙ አክናፊ ድሮን።

የሱፐርካም ድሮኖች ዋና ዋና ባህሪያት፦

🟧 ለተጠበቀ የመረጃ ልውውጥ አስተማማኝ የግንኙነት ሥርዓት።

🟧 የቅኝት ክልልን ለማስፋት የሚያስችል አቅጣጫ ቀያሪ የማሠማራት አቅም።

🟧 በተለያዩ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦች ወይም በኤሌክትሮኒክ ጦርነት ወቅት የተረጋጋ ግንኙነትን የሚያረጋግጥና የርቀት ገደቦችን የሚያልፍ ሰፊ የቅኝት ክልል።

እነዚህ ድሮኖች በዓረብ ሀገራት ለድንበር ጥበቃ፣ ለሕግ ማስከበር፣ ለፀረ-ሽብር ዘመቻዎች እንዲሁም ለነዳጅ ኩባንያዎች፣ ለግንባታ፣ ለእርሻ፣ ለማዕድን እና ለኤሌክትሪክ መስመሮች ክትትል ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

ከሰው አልባ ሥርዓቶች ቡድን የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0