የኮንጎ የመንግሥት ደጋፊ ኃይሎች የኤም23 አማፂያን መውጣታቸውን ተከትሎ ወደ ኡቪራ ከተማ መግባታቸው ተዘገበ
የኮንጎ የመንግሥት ደጋፊ ኃይሎች የኤም23 አማፂያን መውጣታቸውን ተከትሎ ወደ ኡቪራ ከተማ መግባታቸው ተዘገበ
ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ኃይል ጋር የተባበሩት የዋዛሌንዶ ሚሊሻዎች ጥር 10 ቀን በደቡብ ኪቩ ግዛት ወደምትገኘው ኡቪራ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ምንጮችና የኮንጎ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የኮንጎ መከላከያ ኃይል እስካሁን በጉዳዩ ላይ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።
ሚሊሻዎቹ ማለዳ ላይ ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከሰዓት ወደ ከተማዋ ገብተዋል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል። በአንዳንድ ሰፈሮች ነዋሪዎች ደስታቸውን ሲገልፁ መታየታቸው ተዘግቧል።
የኤም23 ጥምረት ከከተማዋ እንደሚወጣ ከቀናት በፊት አስታውቆ የነበረ ሲሆን የሰላም ንግግሮችን ለማመቻቸት የተደረገ "የአንድ ወገን" ውሳኔ እንደሆነ አድርጎ አቅርቦታል።
ይሁን እንጂ የደቡብ ኪቩ ገዥ ዣን ዣክ ፑሩሲ አማፂያኑን፤ ሁከት እና ዝርፊያ ለማደረጀት የሲቪል ልብስ የለበሱ የታጠቁ አባላቶቻቸውን ጥለው ወጥተዋል ሲሉ ከሰዋል።
በከተማዋ ውስጥ ዝርፊያ እና አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፆች መሰማታቸውም ተዘግቧል።
የግዛቱ ባለሥልጣናት ሕዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ይፋዊ መመሪያዎችን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
በ2025 መገባደጃ በኤም23 ቁጥጥር ስር የዋለችው ስልታዊዋ የኡቪራ ከተማ፤ በምስራቅ ኮንጎ ከፍተኛ የጸጥታ ውጥረት በሰፈነበት ወቅት ወደ ኪንሻሳ መንግሥት መመለሷ እንደሆነ ተዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X