ኢትዮጵያ 33.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም አደረገች
16:15 19.01.2026 (የተሻሻለ: 16:24 19.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ 33.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም አደረገች
በሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የአፈርና የውኃ ጥበቃ ሥራ ተጎሳቁሎ ከነበረው 54 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 33.6 ሄክታር መሬት እንዳገገመ የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በየዓመቱ ወደ ወንዞች የሚፈሰው የአፈር መጠን ከ1.9 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ወደ 208 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
ከእርሻ መሬት ላይ በየዓመቱ በሄክታር ይሸረሸር የነበረው 130 ቶን አፈር ወደ 54 ቶን ዝቅ ማለቱንም የሀገር ውስጥ ሚዲያ የሚኒስቴሩን ኃላፊዎች ጠቅሶ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X