የቤኒን ምርጫ ኮሚሽን በጥር ወር የተካሄደውን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ አደረገ
14:46 19.01.2026 (የተሻሻለ: 14:54 19.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቤኒን ምርጫ ኮሚሽን በጥር ወር የተካሄደውን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ አደረገ
አስፈላጊውን ሕጋዊ መስፈርት ያሟሉት “ፕሮግሬሲቭ ዩኒየን ፎር ሪኒውዋል” እና “ሪፐብሊካን ብሎክ” የተባሉት ሁለት ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ሳካ ላፊያ አስታውቀዋል። በዚህም የብሔራዊ ምክር ቤቱን 109 ወንበሮች ብቻቸውን ይጋራሉ።
ፕሮግሬሲቭ ዩኒየን ፎር ሪኒውዋል፦ 41.15 በመቶ ድምፅ በማግኘት ለሴቶች የተያዙ 16 ወንበሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ 60 ወንበሮችን በመያዝ አብላጫነቱን አረጋግጧል።
ሪፐብሊካን ብሎክ ፦ 36.64 በመቶ ድምፅ በማግኘት ለሴቶች የተያዙ ስምንት ወንበሮችን ጨምሮ ቀሪዎቹን 49 ወንበሮች አሸንፏል።
በምርጫው ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በ17,350 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ የሰጡ ሲሆን የድምፅ ሰጪዎች ተሳትፎ 36.73 በመቶ ደርሷል።
ምርጫ ኮሚሽኑ በግምት 87,400 የሚሆኑ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አልባ ሆነው መገኘታቸውን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X