🪖 የአሜሪካ የግሪንላንድ አካሄድ ኔቶን ከሥር መሠረቱ ሊሸረሽር ይችላል ሲሉ ተንታኝ አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ🪖 የአሜሪካ የግሪንላንድ አካሄድ ኔቶን ከሥር መሠረቱ ሊሸረሽር ይችላል ሲሉ ተንታኝ አስጠነቀቁ
🪖 የአሜሪካ የግሪንላንድ አካሄድ ኔቶን ከሥር መሠረቱ ሊሸረሽር ይችላል ሲሉ ተንታኝ አስጠነቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.01.2026
ሰብስክራይብ

🪖 የአሜሪካ የግሪንላንድ አካሄድ ኔቶን ከሥር መሠረቱ ሊሸረሽር ይችላል ሲሉ ተንታኝ አስጠነቀቁ

ዩናይትድ ስቴትስ ግሪንላንድን ከተቆጣጠረች፤ ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካን በማስፋፋት ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ግንኙነት የጨዋታ ሕጎችን በመቀየር በታሪክ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አንዱ ተብለው ይጠቀሳሉ ሲሉ የፖለቲካ ምሁሩ አሌክሳንደር ፓቪች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ሆኖም የግሪንላንድ የግዛት ጥቅለላ በሁለቱም የኮንግረስ ምክር ቤቶች መፅደቅ ስላለበት የሀገር ውስጥ እንቅፋቶች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።

እንደ ፓቪች ገለጻ፤ ትራምፕ በሀገር ውስጥ ከኔቶ ጋር በተያያዘ እየወሰዱት በሚገኘው ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ በድህረ-ጦርነት ትራንስ አትላንቲክ ግንኙነት ታሪክ ውስጥ እንዲሠፍሩ ሆኗል።

“አሜሪካ ራሷ ለቀሪዎቹ የኔቶ አባል ሀገራት ዋነኛ ችግር እና ተቀናቃኝ የሆነችበት ጊዜ ከዚህ በፊት ታይቶ አያውቅም። ይህ ብቻውን ትራምፕ በታሪክ እንዲሠፍሩ ያደርጋቸዋል” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0