የኢትዮጵያውያን የጥምቀት አከባበር ምን ልዩ ያደርገዋል?

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያውያን የጥምቀት አከባበር ምን ልዩ ያደርገዋል?
የኢትዮጵያውያን የጥምቀት አከባበር ምን ልዩ ያደርገዋል? - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.01.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያውያን የጥምቀት አከባበር  ምን ልዩ ያደርገዋል?

ከሌሎች ሀገራት በተለየ በኢትዮጵያ የጥምቀት አከባበር የተለየ እንደሆነ የሚናገሩት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሥነ-ልቦና መምህሩ ቆሞስ አባ ጌዲዮን ብርሃነ ናቸው። 

ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ሦስት ምክንያቶችን ለአብነት አቅርበዋል፦

ታቦት፦ "ኢትዮጵያ ላይ የሚለየው አንደኛ ታቦታት መውጣታቸው ነው። ታቦት የእምነት ማዕከል ወይም ስርዓተ አምልኮ ማዕከል ነው። ከሌሎቹ ኦርቶዶክሶች የሚለይበት ይሄ ታቦት፤ ታቦተ ምስዋዑ መኖሩ ነው።"

ዝማሬ፦ "የዝማሬው ስርዓት ከሌሎች ኦርቶዶክሳውያን የተለየ ነው። የእኛ የከበሮ ትንሽ ሞቅ ያለ ነው፣ ደመቅ ያለ ነው። ያሬዳዊው ስርዓትም አለ።" 

የታቦት አከባበር ስርዓቱ፦ "በሦስተኛ ደረጃ ማታ አውጥቶ በዓሉን የመመስከር ኩነት መከናወኑ፤ እነዚህ ሦስቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውን የጥምቀት አከባበር ልዩ እንዲሆን ያደርገዋል።

“የጥምቀት በዓል አከባበር እንግዲህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን እጅግ ደማቅና ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በዩኔስኮ ጭምር የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ነው። ይህ በዓል ከሐይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር፣ ባሕልን የሚያስተዋውቅ እና የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለዓለም የሚያሳይ ነው።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0