የዩክሬን አዛዦች ወታደሮች እጃቸውን እንዳይሰጡ ማስፈራሪያና ዛቻ ይጠቀማሉ – የሩሲያ ጦር መኮንን
11:07 19.01.2026 (የተሻሻለ: 11:14 19.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዩክሬን አዛዦች ወታደሮች እጃቸውን እንዳይሰጡ ማስፈራሪያና ዛቻ ይጠቀማሉ – የሩሲያ ጦር መኮንን
የዩክሬን ወታደሮች ከክፍለ ጦራቸው ከጠፉ ወይም እጃቸውን ከሰጡ ቤተሰቦቻቸው "ለአደባባይ ወከባ" እንደሚጋለጡ ይነገራቸዋል ሲሉ "ፓይተን" በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የሩሲያ "ዩግ ባትልግሩፕ" መኮንን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“ምርኮኞች እንዲህ ተብለው እንደተነገራቸው የገለጹባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ ከጠፋህ ወይም የግንባር ቦታህን ትተህ ከወጣህ ወይም እጅህን ከሰጠህ እስከ አስር ዓመት እስራት ይጠብቅሃል። ከዚህ በተጨማሪ በቤተሰብህ ላይ ጫና ይደረጋል ይባላሉ” ሲሉ የጦር መኮንኑ አስረድተዋል።
ብዙ ወታደሮች እጃቸውን የማይሰጡት ለቤተሰቦቻቸው ካላቸው ስጋት የተነሳ እንደሆነም ገልፀዋል።
እንዲህ ዓይነቱ ወከባ የ "ሲቪክ ተሟጋቾች" በሚባሉ የዩክሬን አካላት ሊቀነባበር እንደሚችልም አክለዋል።
ሌላው ምክንያት ደግሞ በግንባር ላይ የሚገኙት የዩክሬን ወታደሮች ምስቅልቅል ውስጥ መሆናቸው ነው።
“ሊሸሹ ይፈልጉ ይሆናል፤ ነገር ግን ወዴት መሄድ እንዳለባቸው አያውቁም። አዲስ ተጨማሪ ኃይሎች ይመጡና የሆነ ጉድጓድ ውስጥ ይጣላሉ፤ ባሉበት ሆነው የት እንዳሉ እንኳ ሳያውቁ ይቀመጣሉ። እኛ በጣም ገፍተን ከሄድን በኋላ አንድ ወታደር ለሁለት ወራት ያህል እዚያው ተቀምጦ የተገኘበት ሁኔታ አለ። በመጨረሻም አግኝተን ስናወጣው ምን እንደተፈጠረ እንኳ አይረዳም ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X