የናይጄሪያ አየር ኃይል ባካሄደው የተቀናጀ የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሽብርተኞችን ደመሰሰ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ አየር ኃይል ባካሄደው የተቀናጀ የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሽብርተኞችን ደመሰሰ
የናይጄሪያ አየር ኃይል ባካሄደው የተቀናጀ የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሽብርተኞችን ደመሰሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.01.2026
ሰብስክራይብ

የናይጄሪያ አየር ኃይል ባካሄደው የተቀናጀ የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሽብርተኞችን ደመሰሰ

የናይጄሪያ አየር ኃይል "ኦፕሬሽን ሀዲን ካይ" በተሰኘው ዘመቻ፤ በቦርኖ ግዛት አዚር እና ሙሳራም በተባሉ አካባቢዎች የአየር ጥቃት መፈጸሙን የአየር ኃይሉ የሕዝብ ግንኙነት እና መረጃ ዳይሬክተር ኤር ኮሞዶር ኢሂሜን ኢጆዳሜ አስታውቀዋል። ጥቃቱ ሽብርተኞች አቅደውት የነበረውን ጥቃት ከማክሸፉም በላይ ለምድር ጦር ድጋፍ የሠጠ እንደነበር ተገልጿል።

አርብ ማለዳ የአየር ኃይሉ አውሮፕላኖች በአዚር አካባቢ ለቀረበላቸው የድንገተኛ ድጋፍ ጥሪ ምላሽ በመስጠት፤ በዛፎች ስር ተሸሽገው ዳግም ለመደራጀት የሚሞክሩና እያፈገፈጉ የነበሩ ሽብርተኞችን ኢላማ ያደረገ ተከታታይ እና ትክክለኛ የአየር ጥቃት ፈጽመዋል።

ከጥቃቱ በኋላ በተደረገ ግምገማ ቀሪ ስጋት አለመኖሩ የተረጋገጠ ሲሆን ከጦር ሠራዊቱ፣ ከአካባቢው ባለሥልጣናት እና ከማኅበረሰቡ የተገኘው መረጃ፤ የሽብር እንቅስቃሴው በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን እና በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መመለሱን አመላክቷል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0