ጎንደር "የዐፄዎቹ መታሰቢያ ሽልማት" የተሰኘ ሀገራዊ ዕውቅና መስጫ ሥነ-ሥርዓት ይፋ አደረገች
18:52 18.01.2026 (የተሻሻለ: 19:04 18.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጎንደር "የዐፄዎቹ መታሰቢያ ሽልማት" የተሰኘ ሀገራዊ ዕውቅና መስጫ ሥነ-ሥርዓት ይፋ አደረገች
🟠 አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ እና የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ለመጀመሪያ ግዜ የተከናወነው የእውቅና ሽልማት ከተበረከተላቸው ቀዳሚዎቹ ግለሰቦች መካከል ሆነዋል።
በጥበባት፣ በስፖርት፣ በባሕል እና በተለያዩ ዘርፎች ለሀገራቸው ጉልህ አሻራ ያኖሩ ግለሰቦች አውቅናውን አግኝተዋል።
▫ የኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄ፣ ሰዓሊ ወርቁ ማሞ እና የታሪክ ምሁር አሜሪተሰ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በሙያ መስካቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዕውቅና ያገኙ ሌሎች የሀገር ባለውለታዎች ሆነዋል።
የክብር እውቅናውን ሀገራዊ የማድረግ ዕቅድ እንዳለ "ኢትዮጵያን በጎንደር የባሕል ሳምንት" ላይ በተካሄደው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


