በትራምፕ የሥልጣን ዘመን ግሪንላንድን የመግዛት ሃሳብ ‘የረቂቅ ጂኦ-ፖለቲካዊ ስሌት መገለጫ’ ነው - ቱርካዊ ባለሙያ

በትራምፕ የሥልጣን ዘመን ግሪንላንድን የመግዛት ሃሳብ ‘የረቂቅ ጂኦ-ፖለቲካዊ ስሌት መገለጫ’ ነው - ቱርካዊ ባለሙያ
ትራምፕ ግሪንላንድን ወደ አሜሪካ ግዛት ከቀላቅሉ፤ የአሜሪካን ስፋት፣ ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ታሪካዊ ስኬት ይሆናል ሲሉ የውጭ ፖሊሲ ባለሙያው ሌቬንት ኤርሲን ኦራሊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"ይህ ትራምፕ አወዛጋቢ በሆኑ ንግግሮቻቸው ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ጂኦ-ፖለቲካዊ ስኬቶቻቸውም በታሪክ የሚዘከሩ መሪ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል" ብለዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ ግሪንላንድ በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ለአሜሪካ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አላት፦
◾ ኢነርጂ እና ተፈጥሮ ሀብት፦
በበረዶ መቅለጥ ምክንያት በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ ብርቅዬ የምድር ማዕድናት፣ ዘይት፣ ተፈጥሮ ጋዝ እና ሌሎች ማዕድናት በብዛት ይገኛሉ።
ለዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለላቁ ቴክኖሎጂዎች ወሳኝ የሆኑ ብርቅዬ ማዕድናት፤ አሜሪካ በቻይና ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ ይረዳታል።
ግሪንላንድ ለኢኮኖሚያዊ ሀብት ብቻ ሳይሆን የጂኦ-ኢኮኖሚያዊ ማጠንጠኛ መሳሪያም ሆና ታገለግላለች።
◾ ዓለም አቀፍ ሎጂስቲክስ፦
የአርክቲክ በረዶ መቅለጥ በእስያ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ መካከል አጭር እና ርካሽ የንግድ መስመሮችን ይከፍታል።
የግሪንላንድ ማዕከላዊ ቦታነት ለወደፊት የአርክቲክ መርከብ ጉዞ እና ለዓለም አቀፍ ንግድ ወሳኝ ያደርጋታል።
◾ ወታደራዊ-ስትራቴጂካዊ ደህንነት፦
ለአሜሪካ የራዳር እና ሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶች እንደ ስትራቴጂካዊ የጦር ሰፈር ሆና ታገለግላለች።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ጀምሮ ደሴቲቱ ከሰሜን የሚመጡ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ በአሜሪካ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ወሳኝ ሚና ስትጫወት ቆይታለች።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X