የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ራሷን በሀገርነት ካወጀችው የሶማሊላንድ አስተዳደር ጋር የሰላም እና ውይይት ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ራሷን በሀገርነት ካወጀችው የሶማሊላንድ አስተዳደር ጋር የሰላም እና ውይይት ጥሪ አቀረቡ

ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጥሪውን ያቀረቡት፤ የሰሜን ምስራቅ ግዛት ፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት በክልሉ ዋና ከተማ ላስ አኖድ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት ንግግር፤ ሁሉም የፌዴራል ግዛቶች እኩል መብት እንዳላቸው አፅንኦት በመስጠት፤ የሀርጌሳ አስተዳደር ለሰላም፣ ለውይይት እና ለወንድማማችነት ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ሐሰን ሼክ መሐሙድ አክለውም እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል። የሶማሊያ አንድነት "ለድርድር የማይቀርብ" እና "ቀይ መስመር" መሆኑንም በድጋሚ አስረግጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ ስለ ሶማሊያ ሕዝብ አንድነት ሲናገሩ፤ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ሶማሊያውያን እና ምሁራን በክልሉ መልሶ ግንባታ እና ልማት ላይ እንዲሳተፉ ጋብዘዋል።

ከሶማሊላንድ ጋር ድንበር የሚጋራው የሰሜን ምስራቅ ግዛት ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ይገኛል። የግዛቱ አስተዳደር እ.ኤ.አ በ2023 የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ ታማኝነቱን ለሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት በመግለጽ እና ወደ ፌዴራል ስርዓቱ በመቀላቀል ከሶማሊላንድ መለየቱን አውጇል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0