ትራምፕ ግሪንላንድን ካገኙ ለአሜሪካ በታሪክ ትልቁ የመሬት ይዞታ ይሆናል ተባለ
16:28 18.01.2026 (የተሻሻለ: 16:34 18.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ ግሪንላንድን ካገኙ ለአሜሪካ በታሪክ ትልቁ የመሬት ይዞታ ይሆናል ተባለ
እንደ ኒው ዮርክ ፖስት ዘገባ ከሆነ፤ ግሪንላንድን የሀገሪቱ አካል ማድረግ፤ እ.ኤ.አ በ1803 የተፈጸመውን ታሪካዊውን የሉዊዚያና ግዥ በመብለጥ በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ግዙፉ የግዛት ድምር ይሆናል።
ጉልህ የሆኑ ቁጥሮች፦
የሉዊዚያና ግዥ (1803)፦ 2.14 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር፣
የቴክሳስ መቀላቀል (1845)፦ ወደ 1.01 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር፣
የአላስካ ግዥ (1867)፦ ወደ 1.53 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር፣
ግሪንላንድ፦ ወደ 2.17 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር፡፡
አሜሪካ ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት ምንም ዓይነት ጉልህ የሚባል ግዛት ወደ ድንበሯ አልጨመረችም።
የመጨረሻው ትርጉም ያለው የአሜሪካ የግዛት ግዥ የተፈጸመው እ.ኤ.አ.በ1917 ነበር፤ በወቅቱ ዋሽንግተን የቨርጂን ደሴቶችን ከዴንማርክ በ25 ሚሊዮን ዶላር ገዝታለች። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሴንት ቶማስ፣ ሴንት ክሮክስ እና ሴንት ጆን የሚባሉት ደሴቶች የተገዙት በነበራቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ምክንያት የካሪቢያን የባሕር መስመሮችን እና የፓናማ ቦይን መግቢያ ለመጠበቅ ነበር። ደሴቶቹ እስካሁን ድረስ በፌዴራል መንግሥቱ ስር ያሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ያልተቀላቀሉ የአሜሪካ ግዛቶች ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X