ኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን የሚደግፍ ኢንቨስትመንት ባንክ እያቋቋመች መሆኑ ተገለፀ
15:17 18.01.2026 (የተሻሻለ: 15:24 18.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን የሚደግፍ ኢንቨስትመንት ባንክ እያቋቋመች መሆኑ ተገለፀ
የሚቋቋመው ባንክ ሥራ ፈጣሪዎች ሐሳባቸውን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ ችግር በመሠረታዊነት ለመፍታት ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
ባንኩ ተተኪ ምርቶችን ለማምረት፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለመጨመርና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
አክለውም የኢንቨስትመንት ባንኩ በሀገሪቱ ለሚታየው የሥራ ፈጠራ እንቅስቃሴ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X