ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልን በማገለል የጋዛን ጉዳይ ለብቻዋ ይዛለች - ዘገባ
14:19 18.01.2026 (የተሻሻለ: 14:24 18.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልን በማገለል የጋዛን ጉዳይ ለብቻዋ ይዛለች - ዘገባ
ዋሽንግተን የጋዛ እቅድ "ሁለተኛ ምዕራፍ" ትግበራን እያስኬደች እንደሆነና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በ "ጋዛ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ" ምሥረታ ዙሪያ ያማከራቸው እንደሌለ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል።
ኔታንያሁ ባልተለመደ መልኩ እቅዱ "ከእስራኤል ጋር ቅንጅት ያልተደረገበት ነው" በማለት፤ በተለይም ቱርክ እና ኳታር በቦርዱ ውስጥ መካተታቸውን አጥብቀው በመተቸት ጠንካራ ተቃውሞ እንዳሰሙ በዘገባው ተመላክቷል፡፡ ዋሽንግተን ለአቤቱታው በሰጠችው ምላሽ፤ እስራኤል የጋዛን ጉዳይ እንድናስተዳድር የምትፈልግ ከሆነ "እኛ ባልነው መንገድ መሆን አለበት" ብላለች።
ትራምፕ ከኔታንያሁ ጋር የቅርብ ግንኙነት ቢኖራቸውም በዙሪያቸው ያሉ በርካታ ሰዎች ግን በኔታንያሁ ግትር አቋም ደስተኛ እንዳልሆኑ ዘገባው አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X