በአማራ ክልል የንግድ እንቅስቃሴን ያስተጓጉሉ የነበሩ 145 ሕገ-ወጥ ኬላዎች መነሳታቸው ተገለፀ
13:46 18.01.2026 (የተሻሻለ: 13:54 18.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአማራ ክልል የንግድ እንቅስቃሴን ያስተጓጉሉ የነበሩ 145 ሕገ-ወጥ ኬላዎች መነሳታቸው ተገለፀ
ሕገ-ወጥ ኬላዎቹ ከባለሀብቶችና አሽከርካሪዎች አላግባብ ክፍያ በመቀበል ለምርትና አገልግሎት ዋጋ መናር እንዲሁም ለጤናማ የንግድ ሥርዓት መጓደል እንቅፋት ሆነው መቆየታቸውን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም ሙሐመድ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሕገ-ወጥ ኬላ በመጣል ቀረጥ ያስከፍሉ የነበሩ አካላትን ማስቆም በመቻሉ በአሁኑ ወቅት ምርት በነፃነት ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀስና ጤናማ ግብይት እንዲፈጠር ማስቻሉን አስረድተዋል።
በቀጣይም ሕገ-ወጥ ተግባራትን በመከላከል የክልሉን የንግድ እንቅስቃሴ የተረጋጋ እንዲሆን የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸው ተዘግቧል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X