ካፍ በፊፋ ተጽዕኖ የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ወስኗል መባሉን ውድቅ አደረገ
13:05 18.01.2026 (የተሻሻለ: 13:34 18.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ካፍ በፊፋ ተጽዕኖ የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ወስኗል መባሉን ውድቅ አደረገ
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፤ ውሳኔውን በይበልጥ ግልጽ አድርጎ ማስተላለፍ ይቻል እንደነበር፤ ሆኖም የአፍሪካ ዋንጫ የሚካሄድበት ግዜ ከሁለት ዓመት ወደ አራት ዓመት መራዘሙ እንደሚጸና አስታውቀዋል።
ሞትሴፔ፤ የአፍሪካ ዋንጫ ከ2028 በኋላ በየአራት ዓመቱ እንደሚካሄድ እና በ2029 የ "አፍሪካ ሀገራት ሊግ" እንደሚጀመር አረጋግጠዋል። ይህ ለውጥ ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑንና በሂደት የአፍሪካን እግር ኳስ እንደሚያጠናክርም ገልጸዋል።
አፍሪካ በራሷ ልትቆም እንደሚገባና ፊፋን ወይም አውሮፓን (ዩኤፋን) እንደምትከተል ተደርጎ መታየት እንደሌለበት የጠቀሱት ሞትሴፔ፤ ካፍ ደጋፊዎች ጥቅሙን እንዲረዱ ውሳኔዎቹን በተሻለ ሁኔታ ማስረዳት እንዳለበት አሳስበዋል።
በተጨማሪም ውድድሩ ቀደም ሲል በየሁለት ዓመቱ ይካሄድ የነበረው የካፍን 80 በመቶ ገቢ ይሸፍን ስለነበረ ነው ያሉት ሞትሴፔ፤ አሁን ላይ ግን የአፍሪካ ዋንጫ ከድርጅቱ አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ድርሻው እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X