"የጊኒ ሽግግር ጊዜ አብቅቷል" - ማማዲ ዱምቦያ በይፋ ፕሬዚዳንታዊ ቃለ መኃላቸውን ፈፀሙ

ሰብስክራይብ

"የጊኒ ሽግግር ጊዜ አብቅቷል" - ማማዲ ዱምቦያ በይፋ ፕሬዚዳንታዊ ቃለ መኃላቸውን ፈፀሙ

ዱምቦያ የአምስተኛው ሪፐብሊክ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ሆነው ሀገሪቱን ለሰባት ዓመታት ለመምራት ቅዳሜ ዕለት ቃለ መኃላ ፈጽመዋል።

“እኔ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጥኩት ማማዲ ዱምቦያ፤ ሰላም፣ ማኅበራዊ ትስስር እና ብሔራዊ አንድነትን በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ቦታ ለማስጠበቅ […]፤ እንዲሁም የሪፐብሊኩን ተቋማት፣ የግዛት አንድነት እና ብሔራዊ ነፃነት ለማስከበር ቃል እገባለሁ” ሲሉ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል።

በዚህም ሕገ-መንግሥታዊ ተቋማት ከመመስረታቸው በፊት የነበረው የሽግግር ግዜ በይፋ አብቅቷል።

ዱምቦያ፤ እ.አ.አ በ2021 የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴን ከሥልጣን ያስወገደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የሀሪቱን የሽግግር ግዜ ሲመሩ ቆይተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0