በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጤፍ የተዘጋጀ አማራጭ የወተት ምርት ለዓለም ገበያ አስተዋወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጤፍ የተዘጋጀ አማራጭ የወተት ምርት ለዓለም ገበያ አስተዋወቀ
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጤፍ የተዘጋጀ አማራጭ የወተት ምርት ለዓለም ገበያ አስተዋወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.01.2026
ሰብስክራይብ

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጤፍ የተዘጋጀ አማራጭ የወተት ምርት ለዓለም ገበያ አስተዋወቀ

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ኦሪጅናል ቴፍ-ሊ የተሰኘው ምርት፤ ጤፍን ለሰፊው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል።

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን፤ ጤፍ በኢትዮጵያዊያን የአመጋገብ ዘይቤ ውስጥ ያለውን ሰፊ ቦታ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚችሉ የምግብ ስርዓቶች ጥናቶች ላይ ሊያበረክት ስለሚችለው አዎንታዊ አስተዋጽኦ አብራርተዋል፡፡

የጤፍ ወተቱ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ እየተመረተ ቢሆንም በቀጣይ የምርት ሂደቱን ወደ ኢትዮጵያ ለማሸጋገር እንዲሁም የሥራ ዕድልን በማስፋፋት እና በጤፍ ምርት ላይ እሴት በመጨመር በተሻለ ዋጋ ለወጪ ገበያ የማቅረብ እቅድ እንዳለ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጤፍ የተዘጋጀ አማራጭ የወተት ምርት ለዓለም ገበያ አስተዋወቀ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጤፍ የተዘጋጀ አማራጭ የወተት ምርት ለዓለም ገበያ አስተዋወቀ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0