የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ምክር ቤት አቋቋመ
13:01 17.01.2026 (የተሻሻለ: 13:04 17.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ምክር ቤት አቋቋመ
ምክር ቤቱ ለከተማዋ ከንቲባ ተጠሪ ሲሆን የአደጋ ምላሽ ፈንድ፣ ስልታዊ የምግብና ቁሳቁስ ክምችትን እንዲሁም የድንገተኛ ጊዜ አገልግሎቶችን በበላይነት የመምራት ሥልጣን እንደተሰጠው ተጠቁሟል።
የምክር ቤቱ ተልዕኮዎች፦
አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ የመከላከል እና የመዘጋጀት ስራን በቋሚ ተቋማዊ አደረጃጀት መምራት፣
የውጭ እርዳታ እና ልመናን መቀነስ፣
በራስ አቅም ሰው ሠራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን መከላከል፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለምክር ቤቱ በጽሕፈት ቤትነት ያገለግላል።
“ምክር ቤቱ የተረጂነትን አሉታዊ አስተሳሰብ ለመለወጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥም ግንባር ቀደም ሚናውን ለመወጣት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል” ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X