የአፍሪካ ሲዲሲ አወዛጋቢውን እና በአሜሪካ የሚደገፈውን የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ሙከራ በጊኒ ቢሳው አገደ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ሲዲሲ አወዛጋቢውን እና በአሜሪካ የሚደገፈውን የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ሙከራ በጊኒ ቢሳው አገደ
የአፍሪካ ሲዲሲ አወዛጋቢውን እና በአሜሪካ የሚደገፈውን የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ሙከራ በጊኒ ቢሳው አገደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.01.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሲዲሲ አወዛጋቢውን እና በአሜሪካ የሚደገፈውን የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ሙከራ በጊኒ ቢሳው አገደ

በ1.6 ሚሊዮን ዶላር የአሜሪካ ፈንድ በአራስ ልጆች የሚካሄደው አወዛጋቢ ጥናት "ተሰርዟል" ሲሉ የአፍሪካ ሲዲሲ ባለሥልጣን ያፕ ቦም ተናግረዋል።

ጥናቱ በሥነ-ምግባር ረገድ ከፍተኛ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል። ይህም በዓለም ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት ባለበት ሀገር ለተወሰኑ አራስ ሕፃናት ሕይወት አድን የሆነውንና ውጤታማነቱ የተረጋገጠለትን የሄፓታይተስ ቢ ክትባት እንዳያገኙ የሚከለክል በመሆኑ ነው።

ቦም፤ አፍሪካ ሲዲሲ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ምርምሮችን ይደግፋል፤ "ነገር ግን ይህ በተቀመጡ ደንቦች መሠረት መከናወን አለበት" ብለዋል።

የጊኒ ቢሳው ባለሥልጣናት ጥናቱ አሁንም ሊቀጥል እንደሚችል ቢጠቁሙም፤ አፍሪካ ሲዲሲ ግን ያ የሚሆነው በአፍሪካውያን ባለሙያዎች ታግዞ የሥነ-ምግባር መስፈርቶችን በሚያሟላ መልኩ በድጋሚ ሲቀረጽ ብቻ እንደሆነ አሳስቧል።

የአሜሪካ የጤና ባለሥልጣናት በበኩላቸው፤ የጥናቱ ሰነድ እየተሻሻለ እንደሆነ ገልጸው፤ ቀደም ብሎ በውስጥ የተሠራጨው መረጃ የጥናቱን መጨረሻ እንደማይወክል አስተባብለዋል።

የህክምና ባለሙያዎች የጥናቱን መታገድ በደስታ የተቀበሉት ሲሆን ሌሎች ደግሞ ይህ ውሳኔ በአፍሪካ ውስጥ ከሥነ-ምግባር ውጪ ለሚደረጉ የምርምር ተግባራት ጠንካራ ተቃውሞን የሚያሳይ ምልክት ነው ብለዋል።

ℹ በግብዓት እጥረት ምክንያት ጊኒ ቢሳው በአሁኑ ወቅት ሕፃናትን መከተብ የምትጀምረው በስድስት ሳምንት እድሜያቸው ቢሆንም ከ2027 ጀምሮ ግን ሁሉንም ሕፃናት እንደተወለዱ ለመከተብ አቅዳለች። በሀገሪቱ 18 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎች እና 11 በመቶ ሕፃናት በሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ የተያዙ ሲሆን በሽታው በለጋ እድሜ ከተከሰተ ለጉበት ካንሰር እና ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0