የፈረንሳይ ወታደሮችን ወደ ግሪንላንድ የመላክ ሃሳብ ለአሜሪካ የተላለፈ 'ፖለቲካዊ መልዕክት' ብቻ ነው - ፈረንሳዊ ባለሙያ
19:20 16.01.2026 (የተሻሻለ: 19:24 16.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፈረንሳይ ወታደሮችን ወደ ግሪንላንድ የመላክ ሃሳብ ለአሜሪካ የተላለፈ 'ፖለቲካዊ መልዕክት' ብቻ ነው - ፈረንሳዊ ባለሙያ
ወቅታዊው የግሪንላንድ ጉዳይ የፈረንሳይ የጂኦፖለቲካዊ ቅራኔ ማሳያ ነው ሲሉ የ "ስትራቴጂካ" ምርምር ተቋም ዳይሬክተርና ተንታኝ ፒየር-አንትዋን ፕላክቬንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ፈረንሳይ በሌሎች የአፍሪካ አካባቢዎች እና በባሕር ማዶ ግዛቶች ውስጥ እጇ ባለበት ሁኔታ፤ አስቀድሞውኑ አንጻራዊ ስለሆነው የግሪንላንድ ሉዓላዊነት ጥበቃ መግለጫ መስጠቷ የሚጋጭ ጉዳይ ነው" ብለዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ ከሆነ፤ ይህ ቅራኔ የአውሮፓ የጂኦፖለቲካዊ ሚና በከፍተኛ ሁኔታ በማሽቆልቆሉ የመጣ ነው።
"ዓለም አቀፋዊ ውጥረቶች ባየሉበት በዚህ ወቅት፤ ግሪንላንድ እጅግ ስልታዊ ግዛት እየሆነች መጥታለች። በተለይም አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ለመለየትና ለማጨናገፍ አስፈላጊነቷ እየጨመረ ነው" ሲሉ ባለሙያው አስረድተዋል።
ግሪንላንድን የአሜሪካ ሙሉ ግዛት የማድረግ ሃሳብ አዲስ አለመሆኑን ያስታወሱት ፕላክቬንት፤ ዓለም አቀፍ ውጥረቶች በበረቱ ቁጥር በየጊዜው ብቅ ይላል ብለዋል።
ሆኖም በአውሮፓ እና በአሜሪካ መካከል ቀጥተኛ ግጭት ይፈጠራል የሚለውን ግምት "ሊሆን የማይችል" ብለውታል። ግሪንላንድ እጅግ ሰፊ ግዛት በመሆኗ በጥቂት ወታደሮች ብቻ መቆጣጠር የማይቻል መሆኑንም አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X