የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ቤሉሶቭ የ'ዛፓድ' ጦር ቡድንን ጎበኙ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ቤሉሶቭ የ'ዛፓድ' ጦር ቡድንን ጎበኙ

ጉብኝቱን የተመለከቱ ዋና ዋና መግለጫዎች፦

◻ ሚኒስትሩ በ 'ዛፓድ' የጦር ቡድን የዕዝ ማዕከል ባካሄዱት ውይይት በግንባር መስመሩ ስላለው ሁኔታ እና ስለ ጠላት እንቅስቃሴ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

◻ የ 'ዛፓድ' የጦር ቡድን አዛዥ ኮሎኔል ጄኔራል ሰርጌይኩዞቭሌቭ፤ ወታደሮቻቸው ከ320 ኪሎ ሜትር በላይ በሚሸፍን የግንባር መስመር በሁሉም አራት አቅጣጫዎች ንቁ የማጥቃት እርምጃዎችን እየወሰዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

◻ በታኅሣሥ ወር ቡድኑ ኩቼሮቭካ፣ ፖዶሊ፣ ኩሪሎቭካ፣ ኖቮፕላቶኖቭካ፣ ቦጉስላቭካ እና ዲብሮቫ የተባሉ ስድስት ስፍራዎችን እንዲሁም ከ155 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ ግዛትን ነፃ አውጥቷል፤ ሌሎች 10 ሰፈራዎችን ነፃ የማውጣት ዘመቻም ቀጥሏል።

◻ ጄኔራል ኩዞቭሌቭ ጠላት ወደ ከተማዋ ለመግባት ያልተሳካ ሙከራ ቢያደርግም፤ አጠቃላይ የኩፕያንክስ ወረዳዎች በሩሲያ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

◻ ሚኒስትር ቤሉሶቭ ከጉብኝቱ በኋላ በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ወቅት ጀግንነት ላሳዩ ወታደሮች የክብር ሽልማቶችን አበርክተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0