ምዕራባውያን ለዩክሬን ቢሊዮኖችን ሲልኩ፤ የአፍሪካን የቅኝ አገዛዝ የካሳ ጥያቄ አዳፍነዋል - የሩሲያ ባለሥልጣን

ምዕራባውያን ለዩክሬን ቢሊዮኖችን ሲልኩ፤ የአፍሪካን የቅኝ አገዛዝ የካሳ ጥያቄ አዳፍነዋል - የሩሲያ ባለሥልጣን
የቡድን 20 ትንታኔ፤ ዘላቂ የልማት ግቦችን ከማሳካት አንጻር መሻሻል የታየው በ18 በመቶ አመልካቾች ላይ ብቻ እንደሆነ ይገልጻል ሲሉ በቡድን 20 የሩሲያ ተወካይ ማራት ቤርድዬቭ በቴሌግራም ገጻቸው አስፍረዋል።
በተጨማሪም የቡድን 7 ሀገራት ለልማት የሚመድቡትን እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሱ እና እስከ 2026 ድረስ በ28 በመቶ ያሽቆለቁላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል። ይህም በአፍሪካ እና በአጠቃላይ በደቡባዊው ዓለም ላይ ከባድ መዘዝ ያስከትላል። የገንዘብ ድጋፎችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፖለቲካዊ ቅድመ ሁኔታዎች እና ወሳኝ ማዕድናትን ከማግኘት ጋር እየተያያዙ ነውም ብለዋል።
በተመሳሳይ፤ አሜሪካ ለዩክሬን ከላከችው 130 ቢሊዮን ዶላር አብዛኛው ወታደራዊ ድጋፍ እንደሆነና የአውሮፓ ኅብረት ደግሞ 76 ቢሊዮን ዶላር እና ከዚያም በላይ በቀጣይ እንደሚያወጣ የኪዬል ኢንስቲትዩት መረጃን በመጥቀስ ቤርድዬቭ አመላክተዋል፡፡
▫ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የአፍሪካ ኅብረት ታሪካዊ በደሎችን ለመካስ የካሳ ጥያቄ ቢያቀርብም፤ ምዕራባውያን ግን “ለቅኝ አገዛዝ ጉዳት እና ኪሳራ አፍሪካውያን የሚያቀርቡትን ሕጋዊ ጥያቄ ሆን ብለው ችላ ይላሉ” ሲሉ ቤርድዬቭ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X