ኢትዮጵያና ሕንድ በቅመማ ቅመም እና በመድኃኒት ዕፅዋት ዘርፍ በአጋርነት ለመሥራት ተስማሙ
17:45 16.01.2026 (የተሻሻለ: 17:54 16.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ሕንድ በቅመማ ቅመም እና በመድኃኒት ዕፅዋት ዘርፍ በአጋርነት ለመሥራት ተስማሙ
በኢትዮጵያ የሕንድ ኤምባሲ ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቱ ጋር በመተባባር ባዘጋጀው ልዩ መድረክ ላይ ሁለቱ ሀገራት የጀመሩት አጋርነት የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ አቅም ለማሳደግ እና የሕንድን የቴክኖሎጂ ተሞክሮ ለመጠቀም ያለመ ነው ተብሏል።
ዝንጅብል፣ እርድ፣ ቅመሞች እና ማሽላ በልዩ ሁኔታ ትኩረት እንደተደረገባቸው ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ እሴት የተጨመረባቸው እና ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶች ወደ ውጪ እንድትልክ ሕንድ “በጥራት አቢዮት” ያካበተችውን ልምድ በማካፈል ድጋፍ ማድረግ በምትችልበት መንገድ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በተጨማሪም ሀገሪቱ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናን በመጠቀም የምስራቅ አፍሪካ የምግብ ማቀነባበሪያ ማዕከል ለመሆን በቀረፀችው ስትራቴጂ ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡
ይህ አጋርነት በቅርቡ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ባደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት እና የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ “ስትራቴጂካዊ አጋርነት” ለማሳደግ ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X